የጉዞ መግለጫ
ዝርዝር የጉዞ መርሀ ግብር ቀን 1፡ አዲስ አበባ ወደ ደሴ ጉዞው አዲስ አበባ ከጠዋቱ 12፡30 ይጀምራል በደብረ ብርሀን ከተማ አድርጎ ይቀጥላል፡፡ ደጋማውን የደብር ብርሀን ከተማ እንዳለፍን ደብር ሲና የምትባል ከተማ እናገኛለን፣ ደብር ሲና በገብስ ቆሎዋ የታወቀቺ ከተማ ናት ፣ ቆሎ የሚሽጡት ልጆች ትህትናቸው ብቻ ሳትገዙ እንዳታልፉ ያስገድዳል፡፡ ይህ ቦታ ፣ ለምሳ ምቹ ቦታ ነው፣ ጣፍጩን የበግ ጥብስ ምሳ ከበሉ በኋላ ጉዞ ወደ ደሴ ከተማ ይቀጥላል፡፡ የገብስ ቆሎዎን እይበሉ ታይቶ የማይጠገበውን የወሎ መልካም ምድር እያዩ አዳር በውቦቹ ከተማ ደሴ ያሳልፋሉ፡፡ ቀን 2፡ ደሴ ወደ ላልይበላ ከሆቴላችን ቁርስ ከበላን በኋላ ፣ጉዞ ወደ ቅድስ ላልይበላ ይጀምራል፤ እዛም ለመድርሰ 4 ስአት ገደማ ይወስዳል፡፡ ለምሳ ላልይበላ ከተማ ትደርሳላቹሁ፡፡ ቅድስ ላልይበላ ኢትዮጲያዊያን ለዘመናት ክብሯንና ማንነቷን የሚያወሳላትን ታሪክ ያነጸ ስልጣኔ በአለም ሳይስፋፋ ልጆቿ ከአለም ህዝብ በፊት ተሰልፈው እንደንበር የሚናገር ታሪክ አሻራ ያቆመ የእግዚአብሄር ሰው ነው፡፡ እነዚህ ውቅር አቢያተ ክርስቲያናት ከ900 አመት በላይ የማምለኪያ እና የማመስገኛ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛሉ፣ ከምሳ ባኋላ የተወሰኑትን አቢያተ ክርስቲያን እንጎበኛለን፡፡ ወደ ሆቴላችን ተመልስን እራት ከሆቴሉ እንበላለን የቀኑን ድካም ለመቀነስ ፡፡ ቀን 3፡ ተጨማሪ ቀን በላልይበላ ቁርሳችን በሆቴላችን ከበላን በኋላ ወደ ቀሪ ቤተክርስቲያናት በመሄድ ጉብኝታቺን እንቀጥላለን፡፡ ምሳ ቃና ሬስቶራንት ከበላን በኋላ ከስአት በእራስችን በመርጥነው መንገድ መንቀሳቅስ እንችላለን፡፡ ማታ ቤን አበባ ሬስቶራንት በመሄድ እራት እየበላን የመጨርሻዋን የጽሀይ መጥለቅ እየተመለከትን ፤ ወደ ታች ደግሞ እጅግ ሰፊ ሽሎቆን እንዲሁም ከተማዋን የከበቧትን ዉብ ተራሮች እየተመለከት ቆይታ እናደርጋለን፡፡ለአዳር ወደ ሆቴላችን እንመለሳለን፡፡ ቀን 4፡ ከላልይበላ ወደ አዲስ አበባ ቁርስ ከበላን በኋላ ወደ ላልይበላ ኤርፖርት ጉዞችን እናደርጋለን፡፡ ወደ አዲስ አበባ በሚመጣው በርራ እንመለሳለን፡፡ ጉዞው እዚህ አበቃ ጉዞው የሚያካተው
ጉዞው የማያካተው
|
Subscribe to our newsletter!